Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሕንድ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ ሕንድ ገብተዋል።

ጉባዔው “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው፡፡

‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከጉባዔው ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን የሚያጠናክሩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.