Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ገቢውንም ከውሃ ፍጆታ ክፍያ እና ከተለያዩ የገቢ ርእሶች የተሰበሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡

በዚህም በበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ አኳያ 86 በመቶውን ማሳካት ተችሏል ነው የተባለው፡፡

የተሰበሰበው ገቢም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ470 ሚሊየን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው ከአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለገቢ አሰባሰቡ ማደግ የክፍያ ስርዓት ተደራሽነት እና ዘመናዊነት በማሳደግ ከለሁሉ ክፍያ ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመዘዋወሩ ፣የቆጣሪ ንባብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መታገዙ እና ለበርካታ ጊዜያት ውዝፍ ያለባቸው ተቋማት እና ግለሰቦች እዳቸውን እንዲከፍሉ ከፍተኛ የዘመቻ ስራ መሰራቱ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.