Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራችና መደበኛ ጉባኤ መስከረም 21 እና 22 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች ጉባኤና 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው መስከረም 21 እና 22 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ፤ ይህ የምስረታ ጉባኤ ሕዝቡ ፈተና ሳይበግረው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በነቂስ ወጥቶ ይሆነኛል ያለውን ተወካይ የመረጠበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመጪው ሐሙስ እና አርብ በሚካሄደው መስራችና መደበኛ ጉባኤ ላይ ልዩ ልዩ ሹመቶች ቀርበው እንደሚፀድቁ ጠቁመዋል፡፡

7ኛው ዙር የክልሉ ምክር ቤት ስብጥር ጥሩ መሆኑን ገልጸው፤ ምክር ቤቱ የሕዝብን ፍላጎትና ስሜት በመገንዘብ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.