የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤንም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ያቀረቧቸው አራት ሹመቶች አጽድቋል።
በዚህም የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
እንዲሁም አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል።
አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ከዚህ በተጭዕማሪ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል።
ከንቲባዋ የተሿሚዎቹን የሥራ ልምድና ብቃት ለከተማዋ ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ፣ ምክር ቤቱ ሹመቶቹን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።