የክልሉን እምቅ ሃብት በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል – አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) እምቅ ሃብቶችን በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት ትልቅ እመርታ ተመዝግቧል አሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፡፡
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባዔ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡
አቶ ሙስጠፌ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በመደመር መንግሥት የልማት እሳቤዎች ባለፉት ዓመታት በክልሉ እመርታዊ ስኬቶች መመዝገባቸውንና በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለላቀ ስኬት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
የክልሉን እምቅ ሃብቶች በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት ትልቅ እመርታ መመዝገቡን ገልጸው÷ ሰላምና ልማትን ከማረጋገጥ ባሻገር የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር ተችሏል ነው ያሉት።
ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት እሳቤ የመውጣትና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረትም አመርቂ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አመልክተዋል፡
፡
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በተደመረ አቅም በተለያዩ የልማት መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የተቀናጀ ጥረት እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡