Fana: At a Speed of Life!

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ፡ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ሰፊ ግዛት ብቻ ሳይሆን ዘመናትን የተሻገረ ታሪክ፣ በብዙ ትውልዶች የተገነባ ማንነት፣ በችግር ውስጥ ያልተሰበረ ጽናትና ከዛሬ በላይ የሚመለከት ሕዝብ ያላት ሀገር ናት።
ትልቅነት ያለፈውን ማውራት ብቻ አይደለም፤ ያለፈውን ወደ ነገ የመቀየር ብቃት ነው።
ትልቅነት የትናንትን ታሪክ የዛሬ ኃይል አድርጎ የዛሬን እውቀት የነገ ስኬት አድርጎ መገንባት ነው።
እዚህ ላይ የሕዝቡ ትልቅነት ይመጣል፤ ብዙ ቋንቋዎች፣ ብዙ ባሕሎች፣ ብዙ ታሪኮች የያዘው ይህ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ኃይል፣ ብዝሃነቱን ወደጋራ ዕድል መቀየር ሲችል፤ ትልቅ ሕዝብነቱ በቁጥር ሳይሆን በውጤት ይመዘናል።
ራዕይ ደግሞ ይህን ትልቅነት ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያሰባስብ እይታ ነው።
ይህ ርዕይ የሚቀጥለውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የሚመጡትን ትውልዶች የሚያስብ፤ ዛሬ የምንጀምረው ሥራ ነገ የሚታየውን ኢትዮጵያ እንደሚገነባ የሚያምን ነው።
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ!
ይህ የኢትዮጵያ የትናንት ታሪክ ብቻ ሳይሆን የነገ ተስፋ ጭምር ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.