Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) እና ልዑካቸውን ዛሬ አግኝቻለሁ ብለዋል።

‎በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ምክክር ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በሕንድ ካደረጉት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ተከትሎ በተጠናከረ ትብብርና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወዳጅነታችንን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መነጋገራቸውንም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.