Fana: At a Speed of Life!

የጣና ፎረም በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል – የአማራ ክልል ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው 12ኛው የጣና ፎረም በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የአማራ ክልል ፖሊስ።

12ኛው የጣና ፎረም ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ”በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ”በሚል መሪ ሐሳብ በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል።

የክልሉ  ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራልና የኦፕሬሽናል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዘለቀ አለባቸው ይህንን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ፥ 12ኛውን አህጉራዊ የጣና ፎረም በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል ብለዋል።

ከፌዴራል መንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀትና ከማኅበረሰቡ ጋር የተሳኩ ውይይቶችን በማድረግ አስተማማኝ የደህንነት ማዕቀፍ መዘርጋቱንም ጠቁመዋል።

የባሕር ዳር ከተማና አጠቃላይ ክልሉ አሁን ላይ የተሻሻለ የሰላም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ምክትል ኮሚሽነሩ ሕዝቡ ለጸጥታ ተቋማት እያደረገ ያለው ከፍተኛ ድጋፍና ትብብር ለፎረሙ ስኬት ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን አንስተዋል።

እንዲሁም የፎረሙ ተሳታፊዎች ከመድረኩ ጎን ለጎን የጣና ሐይቅ ገዳማትንና በዙሪያው ያሉ የመስህብ ሥፍራዎችን እንዲጎበኙ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.