Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ እየተቀበሉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ እየተቀበሉ ነው፡፡

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ የመቀበል ሥነ ሥርዓት በብሔራዊ ቤተመንግስት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህ መሰረትም ፕሬዚዳንት ታዬ የ16 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ እየተቀበሉ ይገኛሉ፡፡

የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንቱ እያቀረቡ የሚገኙትም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ ቆጵሮስ ሪፐብሊክ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ አየርላንድ፣ ሕንድ፣ ኦስትሪያ፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ማልታ፣ ቻድ፣ የደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ጣሊያን፣ ባርባዶስ፣ ሉክሰምበርግ እና የግሬናዳ አምባሳደሮች ናቸው።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.