ወጣቶች የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ መስራት ይገባቸዋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በርትተው መስራት እንደሚገባቸው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አስተላለፉ።
ለ3 ቀናት በአዳማ ከተማ አባገዳ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር 5ኛው ጉባዔ የመዝጊያ ስነስርዓት ተካሂዷል።
በመድረኩም አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል የስራ ሀላፊዎች፥ አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች፥ አርቲስቶች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።
አቶ ሽመልስ ቀጣዩ ትግል ራስን በኢኮኖሚ መቻል መሆኑን በመግለጽ ወጣቱ ራሱን እንዲያዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ወጣቱ ለሉአላዊነትና ለአንድነታችን ዋጋ ከፍሎ እዚህ ስላደረሰን ምስጋና ይገባዋል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
በአሁኑ ወቅት ትግላችን ድህነትን ማጥፋት ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ወጣቱ ራሱን ለስራ እንዲያዘጋጅ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቄሮና ቀሬን ሲበላ በነበረው የጁንታ መቀብር ላይ ቆመን ይህንን የወጣቶች መድረክ ማካሄዳችን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ወጣቱ በተበታተነ መንገድ ሲታገል መቆየቱን አስታውሰው አሁን ከ3 ሚሊየን በላይ ወጣቶች ተደራጅተው እየሰሩ መሆኑን አስታውሰዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!