የኦሮሚያ የቡና አምራቾች ሕብረት ስራ ዩኒዬን የቡና ፋብሪካውን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የቡና አምራቾች ሕብረት ስራ ዩኒዬን የቡና ፋብሪካን መርቀው ስራ አስጀመሩ፡፡
ዩኒዬኑ ዋን ኮ ኮፊ (ONE-KOO coffee) የቡና ፋብሪካውን ዛሬ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በይፋ አስመርቆ ስራ አስጀምሯል፡፡
የኦሮሚያ የቡና አምራቾች ሕብረት ስራ ዩኒዬን ዋን ኮ ኮፊ (ONE-KOO coffee) ቡናን ቆልቶ፣ ፈጭቶ የሚያሽግ ዘመናዊ የቡና ፋብሪካውን ነው ያስመረቀው፡፡
ዩኒዬኑ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በገላን እና በቡሌ ሆራ ከተሞች ያስገነባዉን ፋብሪካ እና ዘመናዊ የቡና መጋዘን አስመርቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!