ጠ/ሚ ዐቢይ “ቆሜ ልመርቅሽ” በሚል በሸገር ወዳጅነት ፓርክ ጥላሁንን የሚዘክር ኮንሰርት ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ቆሜ ልመርቅሽ” በሚል በሸገር ወዳጅነት ፓርክ የሚደረገው ዝክረ ጥላሁን ኮንሰርት ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው የዝክረ ጥላሁን ገሠሠን ዝግጅት በማስተባበር፣ የተገኘው ገቢ ለ’ገበታ ለሀገር’ እንዲውል ያደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናዬ እና አድናቆቴ ይድረሳችሁ ብለዋል።
በተጨማሪም ለተሰበሰበው ከ80 ሚሊየን የሚበልጥ ገንዘብ መዋጮ ያደረጋችሁ ሁሉ የማይደበዝዝ አሻራችሁን በኢትዮጵያ ልማት ላይ አሳርፋችኋል ሲሉ አስፍረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!