Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ የሊጉን መሪነት አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት በተካሄደው ጨዋታ ፋሲል ከነማ መሪነቱን አጠናከረ፡፡

ዛሬ ከሰዓት በባህርዳር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሪው ፋሲል ከነማ ጅማ አባ ጅፋር 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ለፋሲል ከነማ ሁለቱን የማሸነፊያ ግቦች ሙጂብ ቃሲም በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡

በዚህም ፋሲል ከነማ በ15 ጨዋታዎች 38 ነጥብ በመያዝ ፕሪምየር ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡

ረፋድ በተካሄደው ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡናን በተመሳሳይ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.