Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2014 በጀት ዓመት 70 ቢሊየን 670 ሚሊየን ብር በጀት ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2014 በጀት ዓመት 70 ቢሊየን 670 ሚሊየን ብር በጀት ወሰነ።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በ2014 በጀት ዓመት ለካፒታል እና መደበኛ ስራዎች፤ የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማስቻል በአጠቃላይ 70 ቢሊየን 670 ሚሊየን 216 ሺህ 28 ብር በጀት በመወሰን ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መርቷል፡፡
የ2014 በጀት ድልድል በ2013 በጀት ዓመት ከተያዘው በጀት ጋር ሲነጻጸር በ9 ቢሊየን 319 ሚሊየን 594 ሺህ613 ብር ወይም የ15 ነጥብ 19 በመቶ ዕድገት አለው ተብሏል፡፡
ከተማ አስተዳዳሩ የቀጣይ 10 ዓመት እና 5 ዓመት መሪ ዕቅድን የተመለከቱ የትኩረት አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂክ ግቦችን መሰረት ባደረገ መልኩ በ2014 በጀት ዓመት ለኮንስትራክሽን ዘርፍ፤ ለውሃና ፍሳሽ ዘርፍ፤ ለመንገድ ልማት ዘርፍ፤ ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ፤ ለትራንስፖርት ዘርፍ፤ የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ፤ ጤና ዘርፍ እና ለቤቶች ልማት ዘርፎች ከፍተኛ በጀት እንደተመደበላቸው ተገልጿል።
በከተማ ደረጃ ለሚገኙ የማዕከል መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው 46 ቢሊየን 559 ሚሊየን 320 ሺህ 315ብር የተመደበ ሲሆን ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 65 ነጥብ 88 በመቶ ድርሻ አለው ተብሏል፡፡
ለማዕከል መስሪያ ቤቶች ከተመደበው በጀት ውስጥ ለመደበኛ ብር 16 ቢሊየን 248 ሚሊየን 362 ሺህ 343 ነጥብ 73 እና ለካፒታል ብር 30 ቢሊየን 310 ሚሊየን 957 ሺህ 972 ብር መደልደሉ ተመላክቷል።
ለክፍለ ከተሞች የተመደበ በጀት ደግሞ 24 ቢሊየን 110 ሚሊየን 895 ሺህ 712 ብር ከአጠቃላይ በጀት 34 ነጥብ 12 % እንዳለው ተገልጿል፡፡
ከዚህ ውስጥ ለመደበኛ በጀት ብር 20 ቢሊየን ፣541 ሚሊየን 879 ሺህ 40ብር እና ለካፒታል ደግሞ 3 ቢሊየን 569 ሚሊየን 16 ሺህ 671 ብር በመሆን ተደልድሏል።
በጀቱን ታክስ ከሆኑና ካልሆኑ፤ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፤ ከሌሎች ምንጮች ማለትም ከብድርና ከዕርዳታ እንዲሁም ካለፈው በጀት ዓመታት ተራፊ ካሽ በጀቱን ለሟሟላት በእቅድ መያዙን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People Reached
200
Engagements
Distribution Score
Boost Post
185
7 Comments
8 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.