በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ 2013 ዓ.ም በጀት አመት ከ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ እንዳሉት÷በ 2013 በጀት አመት ከመንግስት ታክስና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የመንግስት ታክስ በጠቅላላው 1 ቢሊየን 700 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ቢሊየን 658 ሚሊየን 884 ሺህ 776 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡
በዚህም 94 ነጥብ 79 በመቶ አፈፃፀም መመዝገቡንና ይህም አፈፃፀም ከባለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ 22 ነጥብ 48 በመቶ ብልጫ እንዳለው መገለፁን ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
2014 በጀት አመትም ያሉትን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል የድሬዳዋን ተጨባጭ ሁኔታና የፌደራል እቅድን በመጠበቅ የተሻለና የአስተዳደሩን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሊመልስ በሚችል መልኩ ለመስራት ዝግጅት መደረጉ ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!