Fana: At a Speed of Life!

ከዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ጋር በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡
ውይይቱ በቀጣይ በኢንቨስትመንት አካባቢዎች ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ መንግስት ከባለሃብቶቹ ጋር በመሆን ጥናቶችን በማካሄድና አዳዲስ ስልቶችን በማፈላለግ በዘላቂነት አብሮ መስራት በሚቻልበት መንገድ ላይ ትኩረት ማድረጉ ታውቋል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የህግ የበላይነት ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሺባባው መንግስት የተሻለች አገርን ለመገንባት ለውጪ ኢንቨስትመንት ክፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ለሰላምና ጸጥታ ችግሮችም መፍተሄ በማፈላለግ ባለሃብቶች ያለስጋት ወደ ስራ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ዓለማቀፍ ባለሃብቶችም ቀጣይነት ባለው መልኩ ከመንግስት ጋር በመሆን በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለፃቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.