Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሐሰን ታጁ ከኩዌት ፈንድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኩዌት የኢትዮጵያ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሐሰን ታጁ ከኩዌት ፈንድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄኔራል ጋኒም ሱለይማን አል-ጋኒም ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው በኢትዮጵያና በተቋሙ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ሐሰን የኩዌት ፈንድ በኢትዮጵያ ለመንገድ፣ ለኃይል፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና መሰል የመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ለሚያድረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ተቋሙ ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄኔራሉ በበኩላቸው ተቋሙ ለኢትዮጵያ የልማት ፕሮክቶች በሚያደርገው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው÷ ትብብሩን ለማጠናከር ከኤምባሲው ጋር እንደሚሰሩ መግለቸውን ከኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.