Fana: At a Speed of Life!

ገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ሁለተኛውን ስብሰባ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ፖሊሲ በተገቢው ጥናት እና ምርምር ለማዳበር እንዲሁም ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ የተቋቋመው ገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ሁለተኛውን ስብሰባ በበይነ መረብ አካሄዷል።
በዚሁ ስብሰባ ከመንግሥት በኩል የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።
ይኸው የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ከኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ጋር ባካሄደው ሁለተኛ ስብሰባው ባለፉት ወራት የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል።
በዚሁ ስብሰባ ምክር ቤቱ ዶክተር ዓለማየሁ ስዩምን በሰብሳቢነት ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝን በምክትል ሰብሳቢነት እንዲሁም ዶክተር ታደለ ፈረደን በፀሐፊነት መመረጣቸውን አስተዋውቋል፡፡
በቀጣይም የምክር ቤቱን ማቋቋሚያ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ እንዲሁም በህግ ማዕቀፉ ላይ ደግሞ ሰፊ ውይይት አካሄዶ ቀጣይ ሥራዎችን አስቀምጧል፡፡

ምክር ቤቱ ባስቀመጠው አመታዊ ዕቅድ በተለይ መንግስት ቅድሚያ በሚሰጣቸው አጀንዳዎች ላይ ጥናት ላይ የተመሰረተ ምክረ ሀሳብ እንደሚሰጥና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የሚሰራ መሆኑን ከፕላንና ልማት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የምክር ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ እና የመገናኛ ዘዴዎችን በመቅረጽ ዜጎችን የማግኛ መንገዶች እንደሚኖሩም ተነስቷል።
16 አባላት ያሉት የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት የተቋቋመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በታኅሣሥ ወር 2013 እንደነበር ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.