የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተሳካ እንዲሆን ዝግጅት ተጠናቋል- የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተሳካ እንዲሆን ዝግጅት አጠናቆ ወደስራ መግባቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።
ይህ የተባለው ቢሮው በምስራቅ አማራ ከሚገኙ ዞኖች ጋር አረንጓዴ አሻራን አስመልክቶ በኮምቦልቻ ከተማ ባደረገው ውይይት ላይ ነው።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፌ የሆኑት አቶ ወንድየ ማርቆስ እንደተናገሩት በመርሀ ግብሩ በክልል ደረጃ ለመትከል የታቀደውን 2 ቢሊዮን ችግኝ እውን ለማድረግ ሁሉም ዞኖች ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ ገብተዎል ብለዎል።
በክልልሉ የሚገኙ ወረዳዎች ችግኝ የመትከል ስራውን መጀመራቸው የሚበረታታነው ያሉት አቶ ወንድየ የፊታችን ሀሙስ በክልል ደረጃ በአንድ ቀን ከ228 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ገልጸው ለዚህም ቢሮው ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዎል።
በክልሉ ከ18 ሚሊዮን በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኛች መዘገጀታቸው የተገለጸ ሲሆን የአረንጎዴ አሻራ መርሀ ግብሩ የተሳካ እንድሆን ሁሉም አከባቢዎች ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ ገብተዎል ተብሏል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ የክልል የዞንና የወረዳ አመራሮች ከውይይቱ ባሻገር በቃሉ ወረዳ 02 ቀበሌ አረንጎዴ አሻራቸውን ችግኝ በመትከል አሳርፈዎል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!