Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
 
ሰራተኞቹ የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር እየተዋደቀ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የወር ደመወዛቸውን ከመስጠት ባለፈ የደም ልገሳ መርሃ ግብርም አከናውነዋል፡፡
 
የጥራት፣ንግድ አሰራርና ሪጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋ÷ ሰራተኞች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን በተግባር በማስመስከራቸው ለሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስት ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው÷ ሀገርን ከጠላት ለመከላከል በሚደረግ ጥሪ ላይ መሳተፍ እያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታ አለብን ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.