Fana: At a Speed of Life!

ቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ምልምል ወታደሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠናቸውን የተከታተሉ ምልምል ወታደሮችን አስመረቀ፡፡
የማሰልጠኛ ማዕከሉ አዛዠ ኮሎኔል ሰቦቃ በቀለ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ተመራቂዎች መሰረታዊዉን የዉትድርና ሙያ ሙሉ ለሙሉ ማጠናቀቃቸዉን ገልፀዋል ።
ተመራቂዎቹ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢ የተወጣቱ ሲሆኑ÷ በስልጠና ወቅትም የአካል ብቃት ፣ወታደራዊ ሰልፍ ፣ ወታደራዊ ስልቶችንና ሌሎችን ሰልጠናዎች በሚገባና በብቃት ወስደዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
ተመራቂ መሰረታዊ ወታደሮች በበኩላቸዉ÷ስልጠናዉን በብቃት ማጠናቀቃቸዉን ገልፀዉ ÷ሀገሪቱ በምትመድባቸዉ ቦታ ሁሉ በመሰማራት በቆራጥነት ለኢትዮጵያ ዘብ ለመቆም ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል ።
በብስራት መንግስቱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+7
104,420
People Reached
8,610
Engagements
Boost Post
2.8K
71 Comments
148 Shares
Like

Comment
Share
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people standing and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share

0 Comments

 

Published by Tibebu Kebede 1tSofnhSrd 

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከአሜሪካን አምባሳደር የሰብዓዊ ድጋፍን ማጠናከርና ማስፋፋት ላይ ተወያይተዋል
አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከአሜሪካን አምባሳደር ጊታ ፓሲ እና የአሜሪካን ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ጋር የሰብዓዊ ድጋፍን ማጠናከርና ማስፋፋት ላይ ተወያይተዋል።
የውይይቱ አላማ የህውሃት የጥፋት ቡድን ባደረሰው ጥቃት በአማራ እና አፋር ክልሎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ በአፋጣኝ ለማዳረስ እና የመልሶ ማቋቋም ፈጣን ምለሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስልቶችን ለማጠናከር ነው።
ክብርት ሚኒስትሯ በመንግስት በኩል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ከሚገኙ ዜጎቻችንን በተጨማሪ በመላው ሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከቀዬአቸው ርቀው የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ለዚህም የሰብዓዊ አጋሮች ድጋፍ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አመልክተዋል።
አምባሳደር ፓሲ በበኩላቸው እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚከታተሉ መሆኑን ገልጸው የአሜሪካን መንግስት እና ህዝብ ለረጅም ዘመናት የቆየውን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
እየተደረገ ያለው የሰበዓዊ ድጋፍም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ሚ/ር ሾን ጆንስ በበኩላቸው የአሜሪካን ተራድኦ ድርጅት በአማራ እና አፋር ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረገ ያለውን ሰብዓዊ ርብርብ እያገዘ መሆኑንና የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አካባቢዎች ላይ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ድጋፉ በስፋት ተጠናክሮ ይቀጥላለ ማለታቸውን ከሰላም ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

35,816
People Reached
1,068
Engagements

Boost Post

 

 

558

 

17 Comments

38 Shares

 

Like

Comment
Share

17 Comments

View 16 more comments
Oldest



 

  •  

    Ezanas Sayzanas

    ሙፈሪያት ማፈሪያ ከሚል ስም ጋር እየገጠመ ኣስቸገረኝ፤ የትግራይ ህዝብን ኣፍ በመዝጋት እርዳታን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም ለረሃብና ለሞት የዳረገችዉ ሴትዮ ኣሁንም በስመ ወሎ፤ ጎንደርና ኣፋር እህል ዘረፋ ልትጀምር ነዉ። ለነገሩ የተመድና US AID መስራት ካለባቸዉ ተወደደም ተጠላም ከትግራይ ሰራዊት መግባባት ይኖርባቸዋል። ሓሞተ ቢሱ የብልጽግና ሰራዊት የማይቆጣጠራቸዉ ቦታዎች ብዙ ናቸዉ። እና ለ… 

    See More

     

     

    • Like

       

       

     

  • Reply
  • Message
  • 17m

 

Published by Tibebu Kebede 2tSofnhSrd 

 

በወራሪው ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ ነው – ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ
አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ቡድን ወረራ ሳቢያ ከሰሜን ወሎና ከአፋር ለተፈናቀሉ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እየቀረበ እንደሚገኝ የፌዴራል የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽነር ገለጹ።
ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ከፋና ብድሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የትናት ምሽት ዜና መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ለ346 ሺህ 818 ተፈናቃይ ወገኖች ሰብዓዊ ዕርዳታ እየቀረበ ነው።
በዚህም መሰረት ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ ለሚገኙ 118 ሺህ ወገኖች በመንግስት ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን ፣ 60 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በአጋር ድርጅቶች በተለይም ኤፍ.ኤች አይ በሚባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት በኩል ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል ።
በተጨማሪም ለ 92 ሺህ 318 ሰዎች እርዳታ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል ።
አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ቡድን በሚገኝባቸው የሰሜን ወሎ አካባቢዎች የሚኖሩና ከአካባቢው ለመዉጣት ያልቻሉ አቅመ ደካሞች ፣ ህጻናት የሚያጠቡ እናቶችና አካል ጉዳተኞች አሳሳቢ ሁኔታ ዉስጥ መሆናቸውን ጠቁመው ፣ በአለም ምግብ ፕሮግራም በኩል የምግብ ፣ የመድጋኒት ፣ የመጠጥ ዉሃና ሌሎች አቅረቦቶች በአፋጣኝ እንዲደርሱ ስምምነት ላይ መድረሳቸዉን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት ።
የአልም አቀፍ ህግን ተከትሎ ስራዉን እንዲያከናዉን ከአለም ምግብ ፕሮግራም ጋር ስምምነት ላይ በመድረሳቸውም ከመስከረም 5 ቀን 2014 ጀምሮ የእርዳታ አቅርቦቱን ከኮምቦልቻ ማጓጓዝ መጀመሩን አስረድተዋል ።
በሌላ በኩል በሰሜን ወሎ ለሚገኙ 11 ሺህ 500 ለሚሆኑ ዜጎች ፣ በሰሜን ጎንደር ለሚገኙ 119 ሺህ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል ።
በሰሜን ወሎም ሆነ በአፋር አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ እዚህ ግባ ሚባል አይደለም ያሉት ኮሚሽነሩ ፣ የእርዳታ አቅርቦት ስራዉን ለማቀላጠፍና ለማሳለጥ በባህርዳር ፣ በጎንደር ፣ በደሴና በሰመራ የእርዳታ ማስተባበሪያ ማእከላት መቋቋማቸዉን ነው ያስታወቁት ።
የእያካባቢው አስተዳደሮች ፣ የሚመለከታቸው የክልል ሴክተር ቢሮዎችና የፌዴራል ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ተወካዮች የሚገኙባቸው እነዚህ ማእከላት የሰብዓዊ እርዳታው በፍጥነት እና በትክክል ለተረጂዎች እንዲደርስ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል ኮሚሽነሩ ።
የአፋር ክልልን በተመለከተ ሁሉም አካባቢዎች ከወራሪው ሃይል ነጻ መዉጣታቸውን አውስተው በአሁኑ ጊዜ በክልሉ ከ76 ሺህ 500 በላይ ተፈናቃዮች እርዳታ እያገኙ ነው ብለዋል ።
ከሰበዊ ድጋፍ በተጨማሪ በወራሪው ሃይል የወደሙ የጤና ፣ የትምህርትና የዉሃ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና የተፈናቀሉ ባለሙያዎችን በመመደብ ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉም አብራርተዋል ።
የሚገኘውን የእርዳታ አቅርቦት አቀናጅቶ ለተረጂዎች የማድረስ እጥረት እንዳለ የጠቆሙት ኮሚሽነሩ ፣ በተቋቋሙት የአስቸኳይ እርዳታ ማስተባበሪያ ማዕከላት አማካይነት እርዳታውን በፍጥነትና በትክክል ለተረጂዎች ለማድረስ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል ።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በድርቅ በጎርፍ አደጋና በግጭት ምክንያት 11 ሚልዮን የሚሆኑ ዜጎች እርዳታ እንደሚሹም ከኮሚሽነር ምትኩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል ።
በአሰፋ አህመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

May be an image of 1 person and suit

 

34,874
People Reached
671
Engagements

 

Boost Post

 

 

 

325

 

37 Comments

 

14 Shares

 

Like

 

Comment
Share

37 Comments

View 33 more comments

Oldest

 

 

 

 

Published by Tibebu Kebede nt10Sosoredh 

 

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ

 

 

No photo description available.

 

45,801
People Reached
338
Engagements

 

Boost Post

 

 

 

152

 

2 Comments

 

7 Shares

 

Like

 

Comment
Share

2 Comments

View 1 more comment

Oldest

 

 

  •  

     

    ወዲ ደብረጽዮን 

    Follow

     

     

    ዛሬ ቀን ነው 5.035 የሞተ ማለት ነው።

     

     

     


    •  

      Like

       

       

       

     

  • Reply
  • Message
  • 9h

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.