በምግብ እራሳችንን የምንችልበት ጊዜ ቅርብ ነዉ -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ. ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች የግብርና ምርታማነትን በማሻሻል በምግብ እራሳችንን የምንችልበት ጊዜ ቅርብ ነዉ ሲሉ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥ዛሬ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንዲሁም ከቀድምዉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሺመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴን ማሳ ጎብኝተናል ብለዋል።
በጉብኝቱ ከዚህ ቀደም ለእርሻ ያልዋሉ አካባቢዎችን በማልማት ተስፋ ሰጪ ዉጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተመልክተናልም ነው ያሉት ።
በአርሲ ዞን ብቻ በምርት ዘመኑ ከታረሰዉ 680 ሺህ ሄክታር መሬት ዉስጥ 388 ሺህ ሄክታር ያህሉ በኩታ ገጠም የለማ ነው። ይህ ለዘርፉ ትልቅ ጅማሮ ነዉ ብለዋል።
በዚህ ዉጤታማ ስራ ዉስጥ ከክትትልና ድጋፍ አንስቶ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባቹሃል ብለዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share