በምስራቅ አፍሪካ ከባድ ድርቅ ሊከሰት እንደሚችል ተመድ እና ኢጋድ አስጠነቀቁ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በቀጠናው ከባድ ድርቅ ሊከሰት እንደሚችል አስጠነቀቁ።
ሁለቱ ድርጅቶች በጥምረት ናይሮቢ ተገኝተው በሰጡት መግለጫ በምስራቅ አፍሪካ ሊከሰት የሚችለውን ድርቅ ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ይገባል ብለዋል።
ለድርቁ ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለዉ ከተዘረዘሩ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ ኡጋንዳ ፣ ጂቡቲ እና ሱዳን እንደሚገኙበት ሲጂቲኤን ዘግቧል።
እስከ ጥቅምት ወር ድረስ በቀጠናው 26 ሚሊየን ሰዎች ከፍተኛ ለሆነ በምግብ ሰብል ራስን አለመቻል መጋለጣቸውንም ድርጅቶቹ ገልጸዋል።
ድርቁ አሁን ላይ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ አንዳንድ አካባቢች ላይ ጉዳት ማድረሱን የገለጹት ድርጅቶቹ፥ አስከፊ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ግን አስፈላጊው ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!