Fana: At a Speed of Life!

የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ቀናት ብቻ ለመከላከያ ሰራዊቱ 30 ሚሊየን ብር ሃብት በማሰባሰብ ድጋፍ አድረገዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
ድጋፉን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሃይለየሱስ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ አስረክበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ለመከላከያ ሰራዊቱ እያበረከቱ ላሉት የደጀንነት ተግባርም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው አንድነትና ህልውና መጠበቅ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዉ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ህልውና መጠበቅ እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ለመዲናዋ ሰላም መከበር ቀን ከሌት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ለሚገኙት የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የእርድ ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጋቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.