Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ዞብል ክፍለ ከተማ ለህልውና ዘመቻው ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር የዞብል ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ገብረሚካኤል አየልኝ በክፍለ ከተማው በተለያዩ አደረጃጀቶች ለወገን ጦር አገልግሎት የሚውል 15 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን ገለጹ፡፡

በሴቶች አደረጃጀት በክፍለ ከተማው የተለያዩ ቀበሌዎች ስንቅ የማዘጋጀቱ ተግባር በተጠናከረ መንገድ መቀጠሉን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ስንቅ በህዝብ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

በቀጣይም በቀን 14 ኩንታል በክፍለ ከተማ ደረጃ ስንቅ የማዘጋጀት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን ለዚህም ህዝቡ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዛሬ በቸቸላ አካባቢ በተካሄደው የእናቶች ስንቅ ዝግጅት የተገኘው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው እናቶች፥ ጠላትን ለመቅበር በሚደረገው ትግል ከስንቅ ዝግጅት ባለፈ በግንባር እንዘምታለንብለዋል፡፡

ክፍለ ከተማውም በቀጣይነት ለህልውና ዘመቻው ህዝቡን በማሳተፍ የሚያደርገውን ሐብት የማሰባሰብና ስንቅ የማዘጋጀት ተግባር ይቀጥላል ተብሏል።

በምናለ አየነው

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.