የጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ግንባር መዝመት አመራሩን ለዳግም መስዋዕትነት ያዘጋጀዋል – አቶ ወርቁ ሃይለማርያም
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመታቸው አመራሩን ለዳግም መስዋዕትነት እንደሚያዘጋጀው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ሃይለማርያም ገለጹ።
ዋና አስተዳዳሪው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በግንባር ጦርነት መምራታቸው የተግባር መሪ መሆናቸውንና አገራቸውን እንደሚወዱ ከቃል በላይ የገለጹበት ታሪካዊ ውሳኔ ነው ብለውታል።
በኢትዮጵያ ላይ በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ወራሪውን ሃይልን እንደመሳሪያ በመጠቀም ምዕራባውያን የከፈቱትን ጦርነት ለመመከትና የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንደሚቆሙ የዞኑ አመራሮች አረጋግጠዋል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው።
የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች አስቀድመው ወደ ግንባር በመዝመት ህዝቡን በማስተባበር ጠላትን እየተፋለሙ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ማምራት የዞኑ አመራሮች ለዳግም መስዋዕትነት እንዲዘጋጁ አቅም የፈጠረ ነው ብለዋል።
በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዘማቾች ወደ ግንባር ዘምተው ከጠላት ጋር እየተዋደቁ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ወርቁ የቀረው አመራርም መደበኛ የመንግስት አገልግሎት በመስጠትና ደጀን በመሆን አጋርነቱን እየገለፀ መሆኑን አስረድተዋል።
የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ከመሰብሰብ ጀምሮ የዞኑ የመንግስት ሰራተኛና ማህበረሰቡ ሰንቅ በማዘጋጀትና ሀብት በማሰባሰብ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ምዕራባውያንና ወራሪው ሀይል አንገት የሚደፉበት ቀን በጀግኖች ኢትዮጵያውያን እውን እንደሚሆን ገልጸዋል።
በምናለ አየነው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!የእቅድ፣