Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች በራሷ ሙሉ በሙሉ እንደምትፈታ እምነታችን ነው – የባንግላዴሽ አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባንግለዴሽ አምባሳደር ናስሩል ኢስላም ÷ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች ሙሉ በሙሉ በራሷ ለመፍታት የሚያስችላት አቋም ላይ እንደምትገኝ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጦር ግንባር በመገኘት እና ጦሩን በመምራት የህግ የበላይነትን ለማስከበር የተወጡትን ሚና አድንቀው፣ በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በቅርቡ እልባት አግኝቶ ሀገሪቷ ወደ ቀድሞ ሰላሟ ትመለሳለችም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ባንግላዴሽ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት መመስረታቸውን አንስተው በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አምባሳደሩ አንስተዋል፡፡

ባንግላዴሽ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና፣ በወታደራዊ ትብብሮች፣ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች እና በሌሎች በርካታ የትብብር መስኮች ለመሥራት ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ ባንግላዴሽ ከኢትጵያ ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላትም አንስተዋል፡፡

ሀገራቸው በግብርና፣ በመድሐኒት ቅመማ፣ በጨርቃ ጨርቅ ምርት እንዲሁም በሠላምና በደህንነት ዘርፎች በርካታ ልምድ እና እውቀት እንዳላት ገልጸው ፥ ሀገራቸው ልምዳቸውን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ቁርጠኛ መሆኗን አንስተዋል፡፡

ሠላምና ጸጥታን በተመለከተ አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ስለ አዲስ አበባ እንደሚያሰራጩት የሃሰት መረጃ ሳይሆን መዲናዋ እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ እንደ ቀድሞው ሁሉ በሠላም እየተካሄዱ እንደሆነ እርሳቸውም ምስክር መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.