በኮቪድ-19 ክትባት ላይ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ተጽዕኖ አለመኖሩን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮቪድ 19 እና ለኤች አይ ቪ ኤድስ በሚሰጠው የህክምና ሂደት እና ክትባት ላይ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ተፅዕኖ አለመኖሩን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ።
“ኮቪድ-19 በኤች አይ ቪ ኤድስ የማከም ሂደት ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ እና በሃይማኖታዊ አስተምሮ ለመከላከል የሃይማኖት መሪዎች ሚና“ በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ በአሁኑ ወቅት የኮቪድ-19 እና የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የጉባኤው ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደሰ ÷ ለህመሙ መፍትሔ ናቸው ተብሎ በጤና ሚኒስቴር የወጡ ክትባቶችም ሆኑ መድሀኒቶችን ከሃይማኖት እና ከእምነት ጋር በማያያዝ የሚሰራጨው አሉታዊ መረጃ ትክክል አለመሆኑን አስረድተዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ሳቢያ እስካሁን 6 ሺህ 800 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ወረርሽኙን ለመከላከል የሚሰጡትን ክትባቶች በመውሰድ ሂደት ላይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ትልቁን ሚና መውሰዱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በሀገራችን በተፈጠረው ግጭት ቢያ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለኤች አይ ቪ ኤድስም ሆነ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ እንዳይሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
በቅድስት ተስፋየ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!