Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰራዊቱ 54 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት የ54 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እየተፋለመ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት እና የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ሰብሳቢ ዶክተር ለሚ ጎታ÷ ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በድል እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአይበገሬው መከላከያ ሰራዊት ጎን በጽናት እንቆማለን ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት ካደረጋቸው ድጋፎች በተጨማሪ 24 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጅ በበኩቸው ÷ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዋነኛ ስራቸው ዜጎችን በአስተሳሰብና በአመለካከት ቀርጾ ለሃገር ጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑን አውስተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.