Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የሲዳማ ክልልና የሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ነው፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ እየመከሩ ይገኛሉ።

ዛሬ በተጀመረው የውይይት መድረክ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የዞን አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ዝርዝር አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ውይይት አካሄደዋል።

በውይይቱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ ባራሳ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች አመራሮች መሳተፋቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተመሳሳይ የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ተገኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ሀገሪቱ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ መቀልበስና ፍትሕን ማረጋገጥ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
የህልውና ዘመቻው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከመደገፉ በተጓዳኝ የመንግሥት ተቀዳሚ ዓላማ የሆነውን ዘላቂ ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ የአመራር አካላት ዋነኛ አጀንዳ መሆኑንም ገልጸዋል።
እንዲሁም የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከዞንና ከወረዳ ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩዎች ዙርያ ውይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እና የጋምቤላ ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ተጠሪ አቶ ላክደር ላክባክ ተሳትፈዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.