Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን የነበረ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል ዘርፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን ተከማችቶ የነበረ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የእርዳታ ምግብ እህል መዝረፉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
 
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ አሸባሪው ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።
 
በዚህ መሰረትም የሽብር ቡድኑ በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን የነበረና ከ100 ሺህ በላይ ለተፈናቀሉ ዜጎች ለማዋል የተዘጋጀ የምግብ እህል መዝረፉን ተናግረዋል።
 
በኮምቦልቻ ከተማ ኮሚሽኑ 12 መጋዝኖች እንዳሉት የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ የሽብር ቡድኑ አባላት በእነዚህ መጋዝኖች የነበሩ የምግብ እህሎችን ሙሉ በሙሉ መዝረፋቸውን አስረድተዋል።
 
አሁን ላይ በእነዚህ መጋዝኖች ምንም ዓይነት የምግብ እህል ክምችት አለመኖሩን ነው አቶ ደበበ የገለጹት።
 
ከዚህ ባለፈም በመጋዝኖቹ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ የኮሚሽኑ ተሽከርካሪዎችን የሚችለውን ወስዶ የቀሩትን እንዳወደመ ጠቁመዋል።
 
በመላኩ ገድፍ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.