Fana: At a Speed of Life!

“የፈጠርነውን ሀገራዊ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ለሃገር ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል “- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወረራውን ለመቀልበስ የፈጠርነውን ሀገራዊ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ለሃገር ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከንቲባዋ “ከጦርነት ወደ ብልፅግና በሰላም ጎዳና” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ከመዲናዋ አመራሮች፣ ከክፍለ ከተሞች ተቋማት፣ ከመንግስትና ከግል ሚዲያ አመራሮችና ከኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም መምህራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷አሁን ላይ በአሸባሪው ቡድን የተቃጣብንን ወረራ ለመቀልበስ በሁሉም መስክ የፈጠርነውን ሀገራዊ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ለሃገር ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና በሃገር ሁለንተናዊ ልማትና ብልፅግና መረጋገጥ ላይ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል፣ የሚዲያና የኪነ- ጥበብ ባለሙያዉ ሙያዊ ኃላፊነት ትልቅ ነዉ ሲሉን ገልፀዋል ።

ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ ችግሮችን ሁሉን አካታች በሆነ ብሔራዊ የዉይይት መድረክ ለመፍታት እንዲሁም በወራሪው ቡድን የወደሙ አካባቢዎችንና መሰረተ ልማቶችን መልሶ በማቋቋምና በወራሪው ቡድን የተያዙ ቀሪ አካባቢዎችን ነፃ በማድረግ ረገድ የሚጠበቁ ሚናዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል።

የተጎዳዉን ኢኮኖሚ በመገንባትና የብልፅግና ግባችንን በማሳካት በኩል የታየዉን ከፍተኛ ህብረ ብሔራዊ መነሳሳትና አንድነት አሟጦ መጠቀም ከሁላችንም ይጠበቃል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መሰል ውይይቶች በመላው ከተማ በሁሉም ህብረተሰብ ክፍል እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.