አሸባሪው ህወሓት በገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ላይ ውድመትና ዘረፋ ፈጽሟል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ላይ መጠነ ሰፊ ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡
አሸባሪ ቡድኑ ከተማዋን በወረራ ይዞ በቆየበት ጊዜ በየወሩ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠር ብር በመሰብሰብ ለሀገር ልማት በማዋል የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያደርግ በነበረው የኮምቦልቻ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያረጋል ሀይሉ ተናግረዋል፡፡
የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከማውደሙም በላይ የግብር ከፋዮችን እና የሰራተኞችን ማህደር እና ሰነድ ከጥቅም ውጭ በማድረግ ሀገር ማፍረስ የሚለውን ዓላማውን በግልጽ አሳይቷልም ብለዋል፡፡
መዳረሻውን ጥፋት አድርጎ በየደረሰበት ሁሉ ሰይጣናዊ ተግባሩን እያሳየ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤትንም ሶስት መጋዘን ከመዝረፉም በላይ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችንም ሙሉ በሙሉ ማውደሙን የቅርንጫፉ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ገልጸዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹን ወደመደበኛ ተግባራቸው ለማስገባት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ መጠየቁን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!