የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ማዋለድ እና ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ማዋለድ እና ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ሥራ እንዲጀምር ማድረጉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ገለጸ፡፡
ኮሌጁ በጤና ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት በአሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበትን የደሴ አጠቃላይ ሆስፒታል ወደነበረበት ለመመለስና አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ለዚህም ከፍተኛ ስፔሻሊሰት፥ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ነርሶችና እና ሌሎችን የጤና ባለሙያዎች ያካተተ የሕክምና ቡድን በስፍራው ማስማራቱን ነው ኮሌጁ የገለጸው፡፡
በአሁኑ ወቅትም የድንገተኛ የማዋለድ አገልግሎት እና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ማስጀመር መቻሉን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሆስፒታሉ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ሰፈውን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ለሆስፒታሉ አስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶችን እና መድሐኒቶችን በማሟላት መደበኛ አገልግሎቱ እንዲጀምር ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡
የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ቡድን የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ሙሉ ለሙሉ ከመዘርፉም በላይ መውሰድ የማይችለውን ደግሞ አውድሟል፡፡
የሆስፒታሉ ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው መታፈሪያ ቀደም ሲል እንስታወቁት÷አሸባሪ ቡድኑ ስብዓዊ አገልግሎትና ህይወት የማዳን ስራ እየሰራ ባለው የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።
የአሸባሪው ወራሪ ሃይል የሆስፒታሉን መድሃኒት እና የኦክስጅን ማምረቻ ጨምሮ ግዙፍ የህክምና ማሽነሪዎችን ማምረቻ ሙሉ ለሙሉ ዘርፏል የማይችለውንም አውድሟል።
ለሆስፒታሉ የሚያስፈልግ ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልግ በ 976 በመደውል መረጃ ማግኘት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!