በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግን ማንኛውንም ጫና እንደምታወግዝ ሩሲያ ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለኢትዮጵያ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ መርህን እንደምትከተል ገለጸች፡፡
ሩሲያ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች” የሚለውን መርህ እንደምትከተል እና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገልጻለች፡፡
በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችበት ስብሰባ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ላይ የተለያዩ አገራት ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም ሩሲያ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ያላትን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት ማረጋገጧን በመግለጫዋ አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ በመግለጫዋ አክላ እንደገለጸችው ÷ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም የተወሳሰበ እንደመሆኑ መጠን ሁኔታውን ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚደረገውን ሙከራ አሁንም እንደቀድሞው እቃወማለሁ።
ይህም የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ውጤት እንደማያመጣ እንዲሁም ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶችን ለመፍታት አስተዋጽኦ እንደማያደርግ አስታውቃለች ።
በዚህም አገሪቱ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሚል መርህን እንደምትቀበል ገልጻ ÷የአፍሪካ ህብረት ችግሮቹን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት እንደምታደንቅም ነው የገለጸችው፡፡
በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫናም እንደምታወግዝ ሩሲያ በመግለጫው አንስታለች፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዘዴዎች ጋር መተባበሯን የገለጸችው ሩሲያ ÷ ለዚህም ማስረጃው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሙያዊ እና ገለልተኛ ስራ እንደሆነም ጠቁማለች፡፡
የፓሪስን መርሆች ሙሉ በሙሉ ያሟሉ እና ከፍተኛውን የ”ሀ” ምድብ ደረጃ ያላቸው ናቸው ማለቷን በጄኔቫ ከሚገኘነው የሪሲያ ሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!