በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በናይሮቢ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበቃ ወይም #NoMore ንቅናቄ አካል የሆነ እና በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግን የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በኬኒያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው፡፡
በሰልፉ ላይ በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳትፈዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያ ከውስጥ እና ከውጪ የሚደረግባትን ኢ-ፍትሃዊ ጫና ለመቃወም እና ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን የሚያሳዩ መልዕክቶችን አሰምተዋል፡፡
አንዳንድ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያሰራጩትን ሀሰተኛ እና የተዛባ ዘገባም ኮንነዋል፡፡
አሁን ላይ በህዝብ የተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ በመልዕክታቸው ማንጸባረቃቸውንም በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!