Fana: At a Speed of Life!

በጂንካ በ241 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን የጂንካ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ በዘላቂነት መፍታት ያስችላል የተባለለት ከ241 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
 
“የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታዬ ጋንማይ ለግንባታው ዕድል በማግኘታችን በመላው ከተማ ህዝብ ስም እናመሰግናለን” ብለዋል።
 
ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የገለጹት ከንቲባው፥መላው የከተማው ህዝብም ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ።
 
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ በበኩላቸው፥35 በመቶ የሆነውን የንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር መቅረፍ የሚችለውን ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በማስጀመራችን ታላቅ ደስታ ተስምቶናል ብለዋል።
 
የንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ 90 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፥ በ480 ቀን ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል ነው ያሉት ።
 
የበጀቱ ምንጭ ከመንግስትና ከባስከት ፈንድ በተገኘ ብደር እንደሆነ የገለፁት የክልሉ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳኝ፥ ወደ ሥራ የሚገባው የጂንካ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለ20 ዓመታት በዘላቂነት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
 
የጂንካ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ግንባታ በ16 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ በቢሮው ስምምነት መደረጉንም ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.