Fana: At a Speed of Life!

ስለኢትዮጵያ በሚያወጣቸው የሀሰት ትንታኔዎች ምእራባውያን ተከታዮቹን ድንጋጤ ላይ የሚጥለው የህወሃቱ ትሮንቮል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋዜጠኛ ቤሪት አልበርግ በኖርዌይ በሚታተመው ጋዜጦች እና መገናኛ ብዙኃን ላይ የሚወጡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ የትሮንቮል ሐሳቦች ሃይ ባይ ማጣት እንዳሳሰበው ይገልፃል፡፡

ትሮንቮል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት በሰብዓዊነት ላይ ከደረሱ በደሎች 99 በመቶ የሚሆነው በኢትዮጵያ የመንግሥት ኃይሎች እንደተፈጸሙ በጥናቱ ውስጥ እንዲመላከት ማድረጉ እና በቫርት ላንድ ጋዜጣ ማውጣቱም ተመላክቷል፡፡

ጋዜጠኛ ቤሪት አልበርግ፥ አሸባሪ ቡድኑ ህወሓት የህዝብ ድጋፍ ስለሌለው ትሮንቮል እንደገመተው በፈረንጆቹ 1991 ደሴን ተቆጣጥሮ ከሁለት ቀናት በኋላ አዲስ አበባ እንደገባው አሁን ግን ቤተ መንግስት መግባት አልቻለም ብሏል፡፡

“ህወሓት አዲስ አበባን በቅርቡ ይቆጣጠራል” ብሎ ፍራንስ 24፣ ኤን ቲ ቢ እና በመሳሰሉት መገናኛ ብዙኃን ያሰራጨው መረጃም በርካታ ሀገራት እንዲቀበሉት እና ዲፕሎማቶቻቸውን፣ አጥኚዎቻቸውን፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞቻቸውን፣ ሚሲዮኖቻቸውን እና ዜጎቻቸውን ሁሉ ከኢትዮጵያ በፍጥነት እንዲወጡ እንዲያሳስቡ ምክንያት ሆኗቸዋልም ይላል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን እንኳን አዲስ አበባን ሊቆጣጠር ከደሴ መባረሩ ቡድኑን እንዳሳፈረና ምዕራባውያን ደጋፊዎቹን እንዳስደነገጠ ነው የገለጸው፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በርካታ በእጁ የነበሩ ከተሞችን እየጣለ እየፈረጠጠ ይገኛል፤ ትሮንቮል ግን አሁንም አመለካከቱን አልቀየረም ሲልም ትዝብቱን አስቀምጧል ፀሃፊው፡፡

እንዲያውም ይላል ፀሃፊው፥ ትሮንቮል በፖድካስት ሥርጭቱ ለአድማጮቹ በሰጠው ምላሽ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት እንደሚያበቃለት እንዲሁም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ እና የመከላከያ ኃይሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር እንደሚሆን፣ ከዚያም የሽግግር መንግስት እንደሚመሰረት በድፍረት ያለ ሀፍረት ይናገራል ይላል፡፡

አሁን አሁን አሸባሪ ቡድኑ የያዛቸውን ከተማዎች እየለቀቀ በዓለም አቀፉ ሚዲያ ለሽንፈቱ የተለያዩ ምክንያቶችን ማቅረቡ፣ በተሥፋ መቁረጥ የሚፈጽማቸው በደሎች ብሎም የተመዱ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ከኢትዮጵያው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጥምረት ያወጡት የምርመራ ውጤት ህወሓትን መወንጀሉ፣ ቡድኑን የሚደግፉ የአውሮፓ ሀገራት ሽንፈቱን እያመኑ እንዲመጡ እና ተሥፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡

“አሜሪካ ከአሸባሪዎች ጋር አትደራደርም” በሚል መርህ እና መፈክር የምትታወቀው አሜሪካም ኢትዮጵያን ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጋር ተደራደሪ የሚል አማራጭ በፊልትማን በኩል ማቅረቧ እና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ መጣሏ አሜሪካን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ትዝብት ላይ ጥሏታ ሲል ኤሊዜር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ጽፏል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.