Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ በአምስት ወራት ውስጥ ከ479 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በባለፉት አምስት ወራት ከ479 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን፥ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ መሰብሰብ ከሚገባው 521 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ 479 ሚሊየን 417 ሺህ ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 95 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ነው የተናገሩት፡፡

የቢሮው ኃላፊ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ካልሆኑ ገቢዎች ከፍተኛ ገንዘብ ሊሰበሰብ መቻሉን ጠቁመው፥ በዚህም ከቀጥተኛ ታክስ 261 ሚሊየን ብር እንዲሁም ቀጥተኛ ካልሆነ ታክስ ከ156 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አንስተዋል፡፡

ወቅቱ የግብር መክፈያ መሆኑ፣ የተለያዩ ውዝፍ ግብሮች መሰብሰብ መቻላቸውና የዘርፉን ሕጎች ጠበቅ አድርጎ በመስራቱ ይህ ውጤት ሊመዘገብ መቻሉ መገለፁን ከሐረሪ ክልል መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከ196 ሚሊየን ብር በላይ ልዩነት በማሳየት የገቢ እድገት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.