Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ምክንያት የ10 አመቱ የልማት እቅድ ተግዳሮት ገጥሞታል- ፍጹም አሰፋ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአሸባሪው ህዋሃት ወረራ ምክንያት የ10 አመቱ የልማት እቅድ ተግዳሮት ገጥሞታል ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አስፋ ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ሚኒስትሯ፥ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ላይ በመሰረተ ልማቶች እና በሰው ህይወት፣ በግብርና ተቋማት፣ በቱሪዝም ስፍራዎች፣ እንዲሁም በግለሰብ እና በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

በደረሰው ውድመት እና ጦርነቱ በፈጠረው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫና ምክንያት የ10 አመቱ የልማት እቅድ ተግዳሮት እንደገጠመው ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡

አሁን ላይ ቅድሚያ የሚሰጠውን ጉዳይ ጥናት በማድርግ የወደሙ ንብረቶችን መልሶ ማቋቋምና የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው መመለስ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ፥ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ከተከናወኑ በኋላ ሌላ የአጭር እና የረጅም ጊዜ የልማት እቅዶች እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ እና ከጦርነቱ ጎን ለጎን 6 ነጥብ 3 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት መመዝግቡንና የግብርና ዘርፍ ደግሞ ለኢኮኖሚ እድገቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በማክሮ ኢኮኖሚው ዘርፍ ማሻሻያ በማድረግ ለሃገር ውስጥ ምርት ትኩረት መሰጠቱ ሃገሪቱ በጦርነት ውስጥ ብትሆንም የኢኮኖሚ እድገት እንድታስመዘግብ አስተዋፅኦ ማድረጉንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ ተፈጥሮ ሀብቶች ባለቤት ናት ያሉት ሚኒስትሯ፥ የግሉን ዘርፍ ዋና የኢኮኖሚ ተዋናይ ለማድረግ እና ኢንቨስተመንቶችን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት እንደሚመጡ የገለፁ ሲሆን፥ በቅርቡም ሃገሪቱ ያላትን አቅም በመለየት ዳያስፖራዎች የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲመለከቱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ዳያስፖራው ማህበረሰብም በተለያዩ መንገዶች ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በሃገር ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት የቀረበውን እድል በመገንዘብ ወደ ሃገር ቤት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.