Fana: At a Speed of Life!

የአኝዋሃ ዞን በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የአኝዋሃ ዞን በአሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ ኡጁሉ ኝጎዎ እንደገለጹት÷ የዓይነት ድጋፉ የተሰበሰበው በዞኑ ከሚገኙ ከአቦቦ እና ከጋምቤላ ወረዳዎች ነው።
የዞኑ አስተዳደርና ህዝብ የህወሓት የሽብር ቡድን እኩይ ተግባር እስኪቀለበስና ተፈናቃዮቹ ወደ አካባቢያቸው እስኪመለሡ ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እደሚቀጥልም ተናረዋል፡፡
የተሰበሰበው ድጋፍ 1 ሺህ 28 ኩንታል በቆሎ፣ የምግብ ዘይት እና አልባሳት መሆኑን ጠቅሰው በገንዘብ ሲተመን 3 ሚሊየን ብር ይሆናል ማለታቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ካሁን በፊት በአማራ ክልል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ5 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሎው ኡቡፕ በበኩላቸው÷ ሁለተኛ ዙር ከጋምቤላ ወረዳና ከአቦቦ ወረዳ ከተሰበሰበው 1028 ኩንታል ውስጥ 752 ኩንታሉ ከባለሀብቶች የተሠበሠበ ነው ብለዋል።
የህወሓት የሽብር ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት በክልሉ ሲፈጸም ከነበረው ግፍና በደል በተጨማሪ በኢንቨስትመንት ስም የክልሉን መሬት በመቀራመትና መሬቱን ለባንክ በመያዣነት በመጠቀም በቢሊየን የሚቆጠር ገንዝብ ዘርፎ መጥፋቱን ተናግረዋል።
የአቦቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኡሞድ ኡቶው እንዳሉት÷ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለመበታተን የሽብር ተግባራትን ቢፈፅምም ሀገራችን በጀግኖች ልጆቿ ሳትደፈር እንደታፈረች እና እንደተከበረች ለዘላለም ትኖራለች ብለዋል።
ወረዳው ከባለሀብቶች፣ ከአርሶ አደሩ እና ከመንግሥት ሠራተኞች የሠበሰበውን 504 ኩንታል በቆሎ፣ 51 ጀሪካን ዘይትና የተለያየ አልባሳት ወደ አፋር ክልል መላኩንም ገልጸዋል፡፡
የጋምቤላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኡቦንግ ኡዋር÷ የወረዳው ህዝብ ከዚህ ቀደም የተለያየ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰው÷ በቀጣይም የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋ፡፡
በአሁኑ ሰዓትም 479 ኩንታል በቆሎ እና 35 ኩንታል ማሽላ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ድጋፍ ያደረጉ የማህበሰብ ክፍሎችም ድጋፋቸው ተጠናሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.