Fana: At a Speed of Life!

በየጊዜው የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ አደረጃጀቶች በጋራ ሊሠሩ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአካባቢው በየጊዜው የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን መፍታት ያስችል ዘንድ የጎፋ ዞን፣ የደቡብ ኦሞ ዞን እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ማህበረሰቡ ለጋራ ሠላም በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
በጎፋ ዞን፣ በደቡብ ኦሞ ዞን እና በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አዋሳኝ አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው÷ በሦስቱ አጎራባች መዋቅሮች የሚገኙ ህዝቦች በባሕል፣ በወግ፣ በልማድና በልዩ ልዩ እሴቶች ተመሳሳይ የሆኑና ይህንንም ለረዥም ዘመን ጠብቀው የቆዩ በህገወጦችና ወንጀለኞች አጀንዳ እየተቀረፀ አከባቢዎቹ ሠላም እንዲርቃቸው ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
የአካባቢዎቹን ሠላም ማስጠበቅና ወደ ቀደመ ሠላማቸው መመለስ ሀገሪቱ አሁን የገባችበትን ፈተና እንድትወጣ አስተዋፅኦ ያበረክታል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው÷ አመራሩ ከምንጊዜውም በላይ ቆራጥነቱን ማሳየት እንዳለበት ጠቁመዋል።
አሁን ያለንበትን ወቅታዊ ሁኔታ ማሰብና አካባቢዎቻችንን በንቃት መጠበቅ ይኖርብናል ያሉት የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ንጋቱ ዳንሳ ናቸው።
መራሩ አንድ ሲሆን ህዝቡ አንድ ይሆናል፤ ህዝቡ አንድ ሲሆን የገጠሙንን ጥቃቅን ችግሮች በቅንጅት በማለፍ የህዝብ ለህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለንም ብለዋል፡፡
የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ታመነ ታሚርሶ በበኩላቸው÷ “ቀደም ሲል አካባቢያችን የተረጋጋና ሠላም የነበረበት እንዲሁም የእርስ በእርስ ግንኙነቱም የጠበቀና ወንድማማችነት የሚታይበት እንደነበር አንስተዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ለዘላቂ ሠላም መገንባት የጋራ ዕቅድ መንደፍ፣ የውይይትና የዕርቀ ሠላም ኮንፈረንሶችን ማካሔድና የተቋረጡ የማህበረሰብ ግንኙነቶችን ማስቀጠል የአመራሮችና ባለድርሻ አካላት ሚና ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በማቴዎስ ፈለቀ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.