የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች በክልሉ ልማት ላይ የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት በክልሉ ልማት ላይ የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ተጠየቀ፡፡
የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ወደ ክልሉ ለመጡ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች የተዘጋጀው የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
የውይይት መድረኩ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በክልሉ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲገነዘቡና በሁለንተናዊ መስኮች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡
በውይይቱ÷ የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ ጠይብ አህመድ ÷ ሀገራዊ ጥሪውን መሠረት ተከትለው ወደ ሀገራቸው የመጡ የክልሉ ዳያስፖራዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት በክልሉና በሀገር ልማት ላይ የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የውይይት መድረኩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በመድረኩ ላይ በክልሉ ባለው የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ የፓናል ውይይት፣ ጉብኝት፣ የደም ልገሳና ሌሎች መርሀ ግብሮች እንደሚካሄዱ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!