እድሳት ሲደረግለት የቆየው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ነገ ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እድሳት ሲደረግለት የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ነገ ይመረቃል፡፡
ይህ ታሪካዊና የከተማዋ ምልክት የሆነ ህንፃ ከ57 ዓመት በኋላ ለእድሳት የበቃ ሲሆን፥ የከተማዋን የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስም ጭምር መሆኑ ተገልጿል፡፡
የከተማው አስተዳደር ህንፃውን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲታደስ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦም ነው የተሰራው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!