የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ገቡ።
አዲስ አበባ ሲገቡም የመከላከያ ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይ እና የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢቢሲ ዘግቧል።