በጦርነቱ የተጎዱ አርብቶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ስራ በእቅድ ተይዞ ሊሰራ ይገባል ተባለ
አዲስ አበባ ፣ጥር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ የተጎዱ አርብቶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ስራ በእቅድ ተይዞ ሊሰራ እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡
ቋሚ ኮሚቴው፥ በአፋር ክልል በጭፍራ ወረዳ ግመሎች፣ ፍየሎች፣ የእንስሳት መድሃኒቶች፣የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖች እና የአርሶ አደር ሰብሎች መውደማቸውንና መዘረፋቸውን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
አርብቶ አደሩ በድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲማቅቅ የሚያደርገውን የወራሪውን ቡድን ተፅእኖ ለመቀልበስ በተባበረ ክንድ በመስራትና በመተጋገዝ መልሶ የማቋቋም ስራው በእቅድ ተይዞ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሀሙዱ ጋአስ ተናግረዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃ በመሰብሰብ ለተጎዱ አርብቶ አደሮች በጉዳቱ ልክ ፈጥኖ ለመድረስ እና ወደ ነበሩበት መመለስ እንዲቻል በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የአፋር ክልል ርዕሰ መስታዳድር አቶ አወል አርባ፥ ክልሉ በጎርፍ፣ በአንበጣ መንጋ እና በጦርነቱ የተጎዳ መሆኑንና ይህን ችግር ለመቀልበስ ግብረ ሃይል በማቋቋም በጦርነቱ የተጎዱትን አርብቶ አደሮች መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የሰጠውን ሀሳብ በቀጣይ እንደ ግብአትት በመውሰድና እቅድ ውስጥ በማስገባት እንደሚሰራ መገለፁን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!