Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ድርቅ በተከሰተባቸው የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ገለፁ።
በተያዘው ዓመት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቷ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ ‘ላሊና’ የሚሰኝ የአየር ንብረት መዛባት ያስከተለው ነው።
ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በሶማሌ ክልል 9 ዞኖች፣ በኦሮሚያ ክልል የቦረናና የምስራቅ ጉጂ እንዲሁም የሐረርጌና የባሌ ቆላማ አካባቢዎች በድርቁ ተጠቅተዋል።
በደቡበ ክልልም የኮንሶ፣ ጋሞ፣ ጎፋና ወላይታ ቆላማ አካቢዎች እንዲሁም የደቡብ ኦሞ ዞን በድርቁ ተጠቅተዋል።
እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ የድርቅ አደጋው 6 ሚሊዮን በሚጠጉ ዜጎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የብሔራዊ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ የድርቅ አደጋውን መቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ምክክር ማደረጉንም ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።
ድርቁ በተከሰተባቸው ክልሎች በፌዴራል ደረጃ ያለውን አደረጃጀት የተከተለ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ሞሚሽነሩ ጠቁመዋል።
በክልሎች የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከላት በማቋቋም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱንና በመንግስትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል ድጋፎች እየቀረቡ መሆኑንም አክለዋል።
ከምግብ ነክ ድጋፍ ባሻገር የውሃ አቅርቦትና ተንቀሳቃሽ የሰዎችና የእንስሳት ጤና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንና እነዚህን ድጋፎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚጠይቅም ተናግረዋል።
የክልሎች የአደጋ ስጋት የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከላቱን በማጠናከር 24 ሠዓት እንዲሰሩ በማድረግ የድርቅ አደጋውን የመቀልበስ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.