Fana: At a Speed of Life!

ከአምራች ዘርፉ ከ238 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከአምራች ዘርፉ ከ238 ነጥብ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከአምራች ዘርፉ 265 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነው ከ238 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት የተቻለው፡፡
በዚህም የእቅዱን 89 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን ÷ አፈጻጸሙ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ50 ነጥብ 77 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ÷ ዘርፉ በበርካታ ሀገራዊ ችግሮች ውስጥ ቢሆንም የውጪ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ በተሰሩ የማሻሻያ ስራዎች የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ6 ወራት አፈፃጸሙን ከክልልና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ከተጠሪ ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በደሴ ከተማ እየገመገመ መሆኑን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.