Fana: At a Speed of Life!

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ ለመመለስ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አብራሪዎች እና ሌሎች የአየርመንገዱ ሰራተኞች የቦዪንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ለመመለስ እና ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦዪንግ 737 ማክስ የተባለውን የበረራ አውሮፕላን ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ በረራ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መልእክት አስታውቋል፡፡
 
እስካሁን 36 አየር መንገዶች ቦዪንግ 737 ማክስን ወደ ንግድ አገልግሎት የመለሱ ሲሆን ከ 330 ሺህ በላይ የገቢ በረራዎችን እንዳደረጉ ተመላክቷል፡፡
 
የቦዪንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቻችን በኤፍኤኤ( FAA )፣ኢኤኤስኤ (EASA) ፣ ሲኤኤሲ (CAAC) ፣ ኢሲኤኤ( ECAA )እና በሌሎች በርካታ የቁጥጥር አካላት የብቃት ማረጋገጫ ከተሰጣቸው በኋላ ወደ በረራ እንዲመለሱ ይደረጋል ነው ያለው አየር መንገዱ፡፡
 
ደህንነትን ቅድሚያ በመስጠት የሚታወቀው አየር መንገዱ ይህንን በረራ በፍጥነት ለመመለስ ለደንበኞቹ ቃል በገባው መሰረት ከጥቂት ቀናት በኋላ ዝግጁ ሆኖ አገልግሎት እንደሚሰጥ ነው ያስታወቀው፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.