ቢሮው ለሠራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል ስምምነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለሠራተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን ከ9 የሠራተኛ ፌደሬሽኖች፣ ከ10 የአሠሪ አደረጃጀቶች እና 3 አስፈጻሚ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ነው ቢሮው የተፈራረመው፡፡
ስምምነቱ ምቹ የሥራ ሁኔታና አካባቢ በመፍጠር የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተገልጿል።
በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር ዓባይ ባደረጉት ንግግር ፥ ሠራተኞች መብታቸው ሳይሸራረፍ መስራታቸው ምርታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ስምምነቱ ፥ አሠሪና ሠራተኛን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎችና ስምምነቶች ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው በማድረግ ጤናማና ከአደጋ ስጋት ነፃ የሆነ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ነው የተብራራው።
በጀማል አህመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!